ፖለቲካ

ህወሓት ሪፎርም ለማድረግ የሚያስችለው ዝግጅት ማጠናቀቁ አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 02/12/2017፡ የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዛሬ ነሐሴ 02 ቀን 2017 ዓ/ም በሰጡት መግለጫ ፓርቲው ከአስከፊው ጦርነት ጀምሮ ያለውን ሁኔታ በመገምገም ለዚህ መድረክ የሚመጥን ሪፎርም ያደርጋል ብሏል።
ይህን የሪፎርም ስራ የሚመራ ጽሕፈት ቤት እና ኮሚቴ እንደተቋቋመም ገልጿል።

እስካሁን ምሁራንና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ጥናትና ተደርጎ ሰነዶች መዘጋጀታቸውንም የተናገሩት ዶ/ር ደብረፅዮን ማሻሻያው ወደ ህዝብ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ህወሓት በሚቀጥለው ስብሰባ ወጣቱን ያሳተፈ የአመራር ማስተካከያ ያደርጋል፤ ይህንንም ለማሳካት ከአባላቱ ጋር እንደሚሰራ ተናግሯል።

የህወሓት አንዱ አቅጣጫ ከትግራይ ብሄራዊ ፓርቲዎች ጋር ተቀራርቦ መስራት መሆኑ የገለፁት ሊቀ መንበሩ እስካሁንም የተጀመሩ ግንኙነቶች እንዳሉ አብራርቷል።

የትግራይን ሰላም ለማደፍረስ የተቀናጀ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ህወሓት ሁሉንም ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድና በውይይት ለመፍታት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
የፕሪቶሪያ ስምምነት በአግባቡ እንዳይተገበር የፌደራል መንግስት ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን በዚህም በርካታ የክልሉ ህዝብ ለስደትና ሞት እየተደሰገ እንደሚገኝ ገልጿል።
የህወሓት የመጀመሪያ አጀንዳም የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር ማድረግ አንደሆነ ዶ/ር ደብረፅዮን አረጋግጧል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates