ኢትዮጵያኢኮኖሚ

ኢትዮጵያ የግብር አሰባሰቧ እንድትጨምር አይኤምኤፍ አሳሰበ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 29/11/2017፡ የአይኤምኤፍ ዘገባ እንደሚያሳየው፣ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት እያሳየች ብትሆንም፣ የግብር አሰባሰቧ ከሰሃራ በታች ካሉ አገሮች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ መሆኑን ጠቅሷል። ከገቢና ትርፍ የሚገኘው የግብር ገቢም ቢሆን ደካማ መሆኑ ተጠቁሟል።

የአይኤምኤፍ ዘገባ እንደሚያሳየው፣ ኢትዮጵያ በብቃት የግብር ስርዓቷን ብታስተካክል ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርቷ (GDP) እስከ 17% የሚደርስ ገቢ ማግኘት ትችል ነበር፤ አሁን የምታገኘው ግን 8% ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በገንዘብ አሰባሰብ እና አጠቃቀም ላይ ትልቅ ክፍተት መኖሩን ያሳያል።

ሪፖርቱ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የግብር አሰባሰብ መሰረትን በማስፋፋት፣ ከአላስፈላጊ የግብር ነጻነቶች በመውጣትና የግብር አክባሪነትን በማሻሻል ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን ማስቀጠል እንደሚቻል አሳስቧል።

ከፍተኛ የግብር ጫና ዜጎችን ከመደበኛ ሥራ እያራቃቸው ነው ሲልም አይኤምኤፍ አስጠንቅቋል።

በኢትዮጵያ ያለው የግብር ስርዓት፣ በተለይም በዝቅተኛ ገቢ ላይ ባሉ ግብር ከፋዮች ላይ የሚጣለው ከፍተኛ የግብር ተመን፣ ዜጎች ወደ መደበኛ የስራ ዘርፍ እንዳይገቡ ተስፋ እያስቆረጣቸው መሆኑን የአይኤምኤፍ ሪፖርት አመለከተ።

የአለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ ) ባወጣው የቅርብ ጊዜ የግብር ግምገማ ላይ እንዳመለከተው፣ የኢትዮጵያ የግብር ስርዓት አወቃቀር በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ላይ ባሉ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የግብር ተመን የሚጥል ሲሆን፣ ይህም ድርጅቶችና ሰራተኞች መደበኛ ባልሆነው የንግድ መስክ ውስጥ እንዲቆዩ ሊያደርግ ይችላል። ይህ ደግሞ ለልማት የሚውለውን የግብር ገቢ እንዲቀንስ ያደርጋል ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates