በአፍሪካ ቀንድ አዲስ ጦርነትን መከላከል የምትችለው አሜሪካ ብቻ ናት ሲል foreign affairs ዘገበ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 29/11/2017፡ ባለፉት 20 ወራት ውስጥ፣ በመካከለኛው ምስራቅ በርካታ ጦርነቶች ሲቀሰቀሱ፣ የቀይ ባህር ደቡባዊ ጫፍ የአለም አቀፍ ስጋት ምንጭ ሆኗል የሚሉት የፅሑፉ ባለቤቶቹ አሌክስ ዳ ዋል እና ዶ/ር ሙሉጌታ ገ/ህይወት እ.ኤ.አ. በ 2025 የመጀመሪያዎቹ ወራት ውስጥ አሜሪካ በየመን የሁቲዎች ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ ላይ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥታ ጥቃት መፈፀሟ አስታውሷል።
በዚህ ወሳኝ የውሃ አካል ውስጥ ዓለም አቀፍ መርከቦችን በጋዛ ላይ ለደረሰው የእስራኤል ጦርነት ምላሽ ቀጥለዋል የሚለው የፎርየን አፌየርስ ዘገባ ሆኖም የቀጠናው እና የአለም ኃያላን ሀገራት በቀይ ባህር ሌላኛው የባህር ዳርቻ፣ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን ተለዋዋጭ ቀውስ ብዙም ሳይቆይ ወደ ከፍተኛ ግጭት ሊፈነዳ እንደሚችል ችላ ብለዋል ይላሉ።
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ጦርነት ከተነሳ ትግራይ እንደገና ዋና የጦርነት አውድማ ትሆናለች የሚሉት ፀሐፊዎቹ ይህም ለትግራይ እና ለመላው አፍሪካ ቀንድ አስከፊ መዘዝ ይዞ እንደሚመጣ አስጠንቅቋል።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ትልቅ፣ በሚገባ የታጠቀ ጦር ሰራዊት እንዳላቸው በማስታውስ ጉዳቱን ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸው ገልጿል።
ግጭት በቀጠናው ውስጥ ያለውን ደካማ የሰላም እና የፀጥታ ሥነ ሕንፃ ያፈርሷል ያሉት ፀሐፊዎቹ፣ ጦርነቱ ከተነሳ ሶማሊያ እና ሱዳን ሳይቀሩ የዓመፅ አዙሪት ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ገልጿል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኢትዮጵያ፤ ግብፅ ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ቱርክን ወደ ኤርትራ መግባታቸው የበለጠ አለመረጋጋት እየፈጠረ እንደሆነ አስገንዝቧል።
በአሁን ሰዓት ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት የሚገቡበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ እየተደረጉ ያሉት ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በማንሳት ስጋታቸው የሚገልፁት ፀሐፊዎቹ ይህንም ማስቀረት የምትችለው ብቸኛ አገር አሜሪካ እንደሆነች አፅኖት ሰጥቷል።