መካከለኛ ምስራቅአሜሪካ

የአሜሪካ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስለ ጋዛ እና ሱዳን ጉዳይ ተወያዩ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/11/2017፡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዴላቲ ጋር ተገናኝተው ስለ ቀጠናዊ ደህንነት እና በመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ላይ መምከራቸውን ታውቋል።

እሮብ በስቴት ዲፓርትመንት ውስጥ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ሩቢዮ “በሃማስ የተያዙ ታጋቾችን ለማስፈታት የግብፅ ጽኑ ድጋፍ እንደሚሻ” አስገንዝቧል።
እንዲሁም ሩቢዮ እና አብደላቲ ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር መሸጋገር አስፈላጊ ስለመሆኑም መወያየታቸው ተገልጿል።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኤክስ ላይ እንደፃፉት ስብሰባው ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ፣ ቁልፍ ቀጠናዊ ቀውሶችን እና የግብፅን የውሃ ደህንነት ማጠናከርን ያጠቃለለ እንደነበር ነው።

ውይይቱ የተካሄደው ፍልስጤማውያን የምግብ እና እርዳታ እገዳን እየታገሉ ባሉበት በጋዛ ሰርጥ የጅምላ ረሃብን አስመልክቶ የሰብአዊ ኤጀንሲዎች ማስጠንቀቂያ እየጨመረ ባለበት ወቅት ነው ።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates