ኢትዮጵያፖለቲካ

የአፋር ህዝቦች ፓርቲ የሶማሌ ክልልን የወሰነው አዲስ አስተዳደራዊ ማሻሻያ ሕገን የጣሰ ነው ሲል ከሰሰ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/11/2017፡ የአፋር ህዝቦች ፓርቲ በቅርቡ የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 14 አዳዲስ ወረዳዎችን እና 4 አዳዲስ ዞኖችን ለማፅደቅ ያሳለፈውን ውሳኔ የአፋርን ግዛታዊ አንድነት የሚጋፋ እና በሁለቱ ክልሎች መካከል ያለውን ሰላም የሚያደፈርስ ነው ሲል በጽኑ አውግዟል።

ምክር ቤቱ ቅዳሜ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ 14 አዳዲስ ወረዳዎች፣ አራት የዞን አስተዳደር እና 25 የማዘጋጃ ቤት አመራር ጽ/ቤቶችን አጽድቋል። የሶማሌ ክልል አዲሱ መዋቅር ለውጡ “ውስጣዊ ማስተካኪያ መሸረት ያደረገ እና የሌሎች ክልሎች ወሰን በፍፁም ያልነካ ነው” ይላል።

የአፋር ህዘቦች ፓርቲ ውሳኔው እንደገና ብጥብጥ እንዲፈጠር ሊያደርግ እንደሚችል አስጠንቅቋል። “ሀገራችን ከሰሜናዊው ጦርነት በማገገም እና የውስጥ ሰላምን ለማጠናከር በምትጥርበት በዚህ ወቅት ይህ እርምጃ ለሌላ ጦርነት መጋበዝ ነው” ሲል መግለጫው አስጠንቅቋል።

ፓርቲወ ትላንት በሰጠው መግለጫ አዲሶቹ የአስተዳደር አካላት በተለይም “ምእራብ” ወይም “ገልቤድክ ዞን” የሚባሉት የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስተዳደራዊ ድንበሮችን ጥሰዋል ብሏል። “እነዚህ ውሳኔዎች ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት ብቻ ሳይሆኑ አደገኛም ናቸው” ያለው ፓርቲው፣ መልሶ ማዋቀሩ “የክልላዊ ሉዓላዊነትን የሚጥስ” እና ለረጅም ጊዜ የዘለቀ እና ገዳይ የሆነ የድንበር ግጭት እንደገና የመቀስቀስ አደጋ እንዳለው አስጠንቅቋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates