ፖለቲካ

ለሁለት ወራት ታግዶ የቆየውን ሹመት ብአብላጫ ድምፅ ፀደቀ።

ሹመቱ 5 የህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባላት ተቃውሞታል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 24/11/2017፡ ለበርካታ ዓመታት የህወሓት ፅ/ቤት ሓላፊ ሆኖ ያገለገሉት አቶ አለም ገ/ዋህድ ከወራት በፊት ህወሓት ባደረገው የስልጣን ሽግሽግ ከፅ/ቤት ኃላፊነታቸውና ከስራ አስፈፃሚነት እንዲወርዱ መደረጋቸው ይታወሳል።

ጄነራል ታደሰ ወረደ መጋቢት ወር መጨረሻ ፕሬዝዳንት ከሆኑ ከሁለት ወራት በኃላ ያለ ስራ ተቀምጦ የነበሩትን አቶ አለም ገ/ዋህድን በምክትል ፕሬዝዳንት መአርግ የፖለቲካ አማካሪና የዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተማዎችን ክትትል አድርጎ እንደሾመዋቸው ይታወቃል። ሆኖም ሹመቱ በህወሓት ድጋፍ አላገኘም ነበር።

ፕሬዝዳንት ታደሰ መንግስታዊ ሹመት የድርጅት ደጋፍ አያስፈልገውም ቢሉም ሰሚ ሳያገኙ ቆይቷል። አቶ አለምም ጉዳዩ በድርጅት ስብሰባ ቢታይም ችግር እንደሌለባቸው በመግለፅ ድርጅቱ ለሚያካሂደው የማእከላይ ኮሚቴ ስብሰባ ሲጠባበቁ መቆየታቸው ምንጮች ተቁሟል።

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ሰሙኑን ለስብሰባ መቀመጡን ተከትሎ የአቶ አለም ገ/ዋህድ አንድ አጀንዳ ሆኖ መቅረቡን ተሰምቷል። በዚህም በስብሰባው ከተቀመጡ 37 የማእከላይ ኮሚቴ አባላት 25ቱን  የአለም ገ/ዋህድ ሹመትን በመደገፍ አፅድቆታል። 12 የስብሰባው ተሳታፊዎች የአለምን ሹመት የተቃወሙ ሲሆኑ ከእነዚህ 5 ስራ አስፈፃሚ አበላት መሆናቸውን ታውቋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates