ኢትዮጵያኢኮኖሚ

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 8 ቢሊየን ገደማ ችግኞች እንደሚተከሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለፁ።

የአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞች የመትከል መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት መጀመሩ ተገልጿል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 24/11/2017፡ የ2017 የአርንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ   “በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 8 ቢሊየን ገደማ ችግኞች እንደሚተከሉ ገልጿል።

ይህም ባለፉት ሰባት ዓመታት የተተከሉ ችግኞችን መጠን 48 ቢሊየን ማድረስ የሚያስችል ነው” ብለዋል፡፡

በአረንጓዴ አሻራ ዕቅዳችን 50 ቢሊየን ችግኝ መትከል ነው ሲሉም በመህርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሰጠው መግለጫ እንዳስታቀው  ” ባለፈው አመት በአንድ ጀንበር 617 ሚሊየን ችግኞችን ተተክለዋል። ዘንድሮ ይህንን በማሻሻል በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዘመቻው ተጀምሯል” ብለዋል።

“የችግኝ ተከላው አግሮ ኢኮሎጂው በፈቀደው አካባቢ በሙሉ ይከናወናል ያለው ሚኒሴቴሩ” ሁሉም ማህበረሰብ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ ” በመትከል ማንሰራራት ” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ
በዛሬው ዕለት ስለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ”  ትንሽ ትልቅ፣ የከተማ የገጠር ሳንል ዜጎች ሁሉ አካባቢያችን እንዲያገግም፣ የውሃ ምንጮቻችን እንዲጠበቁ፣ የኑሮ ሁኔታችን እንዲሻሻል እንዲሁም ለመጪው ትውልዶች ዘላቂነት ያለው ነገን ለማረጋገጥ የምንሳተፍበት ተግባር ነው ” ብለዋል።

በሚቀጥለው የ 2018 ዓም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ50 ቢሊየን በላይ ችግኞችን በመትከል የሚጠናቀቀው የአረንጓዴ አሻራ በዘንድሮ አመት 7.5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል በእቅድ መያዙን ተጠቁሟል።
ሆኖም የተያዘው ዕቅድ መተጨባጭ መሬት ላይ ይተገበራል ወይ የሚለው ጥያቄ የበርካቶች ነው። እስካሁን የተተከሉት ችግኞች ያሉበት ደረጃም እስካሁን የተካሄደ አሰሳ የለም።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates