አውሮፓ

በሩስያ የተከሰተው የ8.8 ሬክተር ስኬል መሬት መንቀጥቀጥ

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/11/2017፡ በሩሲያ የባህር ዳርቻ የተከሰተውን እጅግ ከፍተኛ የተባለ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በፓሲፊክ ውቅያኖስ ዙሪያ ሱናሚ ይከሰታል በሚል ማስጠንቀቂያዎች እየተሰጡ ነው።

ዛሬ ረቡዕ ማለዳ ላይ በሩሲያ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ የተከሰተውን 8.8 ማግኒቲዩድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በሰሜናዊ ፓሲፊክ ውቅያኖስ ውስጥ በርካታ ሱናሚዎች ይከሰታሉ በሚል ከሃዋይ እስከ ኒውዚላንድ ያሉ ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያዎችን አውጥተዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በጎርጎሮሳውያኑ 2011 በጃፓን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ የደረሰውን ፍንዳታ ካስከተለው የመሬት መንቀጥቀጥ ወዲህ በዓለም ላይ ከተመዘገቡት የመሬት መንቀጥቀጦች ሁሉ ከፍተኛው ነው ተብሏል።

የፓሲፊክ የሱናሚ ማስጠንቀቂያ ማዕከል የመሬት መንቀጥቀጡ በሁሉም የሃዋይ ደሴቶች የባህር ዳርቻዎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ሱናሚ አስነስቷል ብሏል።

የሱናሚ ማስጠንቀቂያዎች ከተላለፉባቸው ሀገራት መካከል ራሽያ፣ ጃፓን፣ ታይዋን፣ ቻይና፣ ሃዋይ፣ ጉአሜ፣ ቶንጋ፣ ካሊፎርኒያ፣ አላስካ፣ ኦሪገን፣ ዋሽንግተን፣ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ፣ ሜክሲኮ፣ ፔሩ እና ኢኳዶር ተጠቃሽ ናቸው።

የፊሊፒንስ ባለስልጣናት በአርኪፔላጎ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ላይ ያሉ ግዛቶች እና ከተሞች ከአንድ ሜትር ያነሱ የሱናሚ ሞገዶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፤ ሰዎችም ከባህር ዳርቻ አካባቢዎች እንዲርቁ መምከራቸውን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ፍራንስ 24 ዘግቧል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates