ኢትዮጵያፖለቲካ

የፌደራል ፖሊስ አስጠነቀቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 18/11/2017፡ “በማህበራዊ ሚዲያ ሀገሪቱን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ በሚዲያ ዘመቻ በሚያካሄዱ ሰዎች ላይ የተጠናከረ ኦፕሬሸን ይካሄዳል” ሲል የፌደራል ፖሊስ አስጠነቀቀ።

የፌደራል ፖሊስ በውጭና በሀገር ውስጥ ሆነው በማህበራዊ ሚዲያ ሀገሪቱን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ የሚዲያ ዘመቻ  በሚያካሄዱት ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ የተጠናከረ ኦፕሬሸን ይካሄዳል ሲል አስታወቋል።

ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር ሙከራ የሚያደርጉ ግለሰቦች እና ቡድኖችን ለሕግ የማቅረብ ሥራን አጠናክሬ እቀጥላለሁም ብሏል።

“በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያ እንዲሁም በሁሉም መግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ አሰሳና ፍተሻ እንደሚካሄድ ገልጿል። ዋነኛ ትኩረቴ “በፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ” ነው ሲልም አክሏል።

ፌደራል ፖሊስ ይህንን ያስታወቀው በቀጣይ ሦስት ወራት (ከሐምሌ 2017ዓ/ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2018። ዓ.ም) በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ሁነቶች ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በተዘጋጀ የፀጥታ ዕቅድ ላይ በተደረገ ውይይት ነው።

በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩትም ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከሪፐብሊካን ጋርድ፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተውጣጡ ስትራቴጂክና ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን ተጠቁሟል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates