
ኢትዮ ሞኒተር፡ 18/11/2017፡ የሰልፉ ዓላማ ሰሙኑን በትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር የተደረገውን የአመራር ሹም ሽር በመቃወም ነው።
የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ ሐምሌ 15 ቀን 2047 ዓ/ም የደቡባዊ ዞን አስተዳደር አመራር የተወሰነ ማስተካከያ እንዳደረጉ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል።
በዚህ የዞኑ አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ሃፍቱ ኪሮስ የማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ አድረጎ ሾሟል። ሆኖም ሹመቱ አልተቀበሉትም። ሹም ሽሩ በፖሊስ የተደገፈ በመሆኑ የዞኑ ሽማግሌዎች ትላንት ወደ መቐለ በመጓዝ ከፕሬዝዳንቱ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ዛሬ ደግሞ የአስተዳደሩ ፅ/ቤት በሚገኝበት ማይጨው ከተማ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በፅ/ቤቱ የነበረው የክልሉ ፖሊስ ሐይል እንዲለቅ እንደተደረገ ተሰምቷል።
ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ ዛሬ ከሰአት ወደ ማንጨው ተጉዞ ክህዝቡ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።