አፍሪካ

ቱርክ ወደ ሶማሊያ ያላከችውን ወታደራዊ ቁሳቁሶች የጫነች መርከብ በፑንትላንድ በቁጥጥር ሥር መዋልዋ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 17/11/2017፡ የሶማሊያ አንድ ግዛት የሆነችው የፑንትላንድ አስተዳደር ከቱርክ ለሶማሊያ መንግሥት የተላኩ ከፍተኛ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን የጫነች መርከብ መያዙ በሁለቱ ወገኖች መካከል ውዝግብ አስከትሏል።

በዚህም የተነሳ የሶማሊያ መንግሥት የፑንትላንድ አስተዳደር በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ወታደራዊ ጭነት የያዘችውን መርከብ መያዙ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ የተፈጸመ ጥሰት እና የባሕር ላይ ውንብድና ፈጽሟል በሚል ወንጅሏል።

የፌደራሉ መንግሥት የማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ የተያዘው መርከብ በሶማሊያ እና በቱርክ መካከል በተደረገው የመከላከያ ትብብር ስምምነት መሠረት የቱርክ ሶማሊያ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ (ቱርክሶም) ንብረት የሆኑ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን እያጓጓዘ ነበር ብሏል።

የአገሪቱ ባለሥልጣናት ጭነቱ በሕጋዊ መንገድ እና የአገሪቱንም ሆነ ዓለም አቀፍ ሕጎችን የተከተለ መሆኑን ተናግረዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates