
ኢትዮ ሞኒተር፡ 17/11/2017፡ የፋኖ ኃይሎች በኦሮሚያ ክልል ተደራጅተው እንደሚንቀሳቀሱ አስታወቁ።
ይሁን እንጂ በክልሉ በቅርቡ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ግድያ ላይ “እጃችን የለበትም” ሲሉ አስተባብለዋል።
የፋኖ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ኖኖ ወረዳ፣ ቆንዳላ ቀበሌ ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ/ም የስድስት ወር ሕፃን ጨምሮ ከ16 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ በተባለው ጥቃት ላይ “እጄ የለበትም” ሲል አስተባብሏል።
በክልሉ በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ኖኖ ወረዳ፣ ቆንዳላ ቀበሌ ሐምሌ 4 ቀን ከ16 በላይ ሰላማዊ ሰዎች “በፋኖ ታጣቂዎች” መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎችና የኖኖ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በወቅቱ መግለፁ ይታወሳል።
የፋኖ አደረጃጀት በክልሉ ታህሳስ 7 ቀን በይፋ ተመስርቶ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ የአይን እማኞች አረጋግጧል። ፋኖ ከአማራ ክልል አልፎ በኦሮምያ እንደሚንቀሳቀስ ቢገልፅም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሰሙኑን ባስተላለፉት መልእክት ግን “ፋኖ አክርካሪው ተመቷል፤ ወገቡ ተሰብራል፤ ተበትኗል” ማለታቸው ይታወሳል።