ኢትዮጵያኢኮኖሚ

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 462 ሺሕ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ተደረገብኝ አለ።

ሆኖም የተደረጉበት ሙከራዎች ምንም አይነት ጉዳት አላደረሱም ብሏል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 17/11/2017፡ ኢትዮ ቴሌኮም የሦስት ዓመት መሪ ስትራቴጂ ማጠቃለያ ሪፕርት እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት ሪፓርት ማጠቃለያ በዛሬው ዕለት በማካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 462 ሺሕ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች እንደተደረጉበት አስታውቋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 1 ሺሕ 683 አዲስ የሞባይል ጣቢያዎች መተከላቸውን የተናገሩት የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ “ይህም በመሆኑ ከዚህ ቀደም የኔትዎርክ እና ሞባይል አገልግሎት የማያገኙ አካባቢዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ያስቻለ ነው” ብለዋል።

“በዚህም ኢትዮ ቴሌኮም ያሉት ታዋሮች ብዛት 10 ሺሕ 10 ደርሷል” ያሉት ሥራ አስፈጻሚዋ፤ ከ1 ሺሕ 683 ውስጥ 954 ጣቢያዎች አገልግሎት በቅርበት የማያገኙ የነበሩ ቦታዎች ላይ የተገነቡ ሲሆን፤ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በ4ጂ ኔትዎርክ 512 ከተሞችን እና በ5ጂ ደግሞ 16 ከተሞችን ማገናኘት መቻሉን ገልጸዋል። የፋይበር ተደራሽነት በተመለከተ በአጠቃላይ 22 ሺሕ 673 ነጥብ 1 መድረሱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 462 ሺሕ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች የተደረጉበት ሲሆን፤ ምንም አይነት ጥቃት እንዳልደረሰበት አስታውቀዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates