አፍሪካ

የሱዳን መንግስት “ዋትስ አፕ” ላይ እገዳ እንደሚጥል አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 15/11/2017፡ የሱዳን ቴሌኮሚኒኬሽንና ፖስታ ባለስልጣን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይህ እገዳ የሚጣለው  “ከአገር ደህንነት” የተነሳ መሆኑን ገልጿል፡፡

በመግለጫው “የአገሪቱን ብሄራዊ ፀጥታና ደህንነት ለማስጠበቅ ቅድመ ጥንቃቄዎች መደረግ ስላለባቸው ይህንን እርምጃ መውሰድ አስፈልጎናል” ያለው ባለስልጣኑ በመሆኑም ከሐምሌ 25 አንስቶ በአገሪቱ ውስጥ የዋትስአፕ አገልግሎትን እንደሚያቋርጥ አስረድቷል፡፡

ከ4 ቀናት በኋላ ይህ አገልግሎት ከመቋረጡ በፊት ሱዳናዊያን እንደልባቸው በዋትስ አፕ መልእክት እየተለዋወጡ እንዲቆዩ ያሳሰበው ባለስልጣኑ “የአገር ደህንነት መቅደም ስላለበት ይህንን እርምጃ በመውሰዳችን ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” ብሏል፡፡ እገዳው የሚቆየው ላልተወሰነ ጊዜ መሆኑንም አስረድቷል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates