ኢትዮጵያፖለቲካ

ትግራይ መገንጠል ትችላለች አሉ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 15/11/2017፡ የመከላከያ ሰራዊት እታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጅማ በተካሄደው የደቡብ እዝ ማጠቃለያ መድረክ ተገኝቶ እንደተናገሩት የህወሓት መሪዎች ተው! በፓርላማ ተው ተብሏቸዋል ሲሉ ተደምጧል።

“ተው ስንላችሁ ሰሜን እዝን መታችሁ፤ ለኢትዮጵያም ለትግራይም ብዙ ኪሳራ አስከተለ” ያሉት ፊልድ ማርሻሉ ጦርነት ከተጀመረ በኃላም ከትግራይ ወጣንላችሁ ተው ስንላችሁ እስከ ሰሜን ሽዋ ተከትላችሁን መጣችሁ ብሏል።

የትግራይ መሪዎች ለሶስተኛ ጊዜ ተው ስንላችሁ ጦርነት ጀምራችሁ ከቸመታችሁ በኃላ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ለመፈሰም ተገደዳችሁ ያሉት ብርሃኑ ጁላ አሁንም ለአራተኛ ጊዜ ተው ብለን እየለመንናችሁ ነው ሲሉ ተደምጧል።

የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግብሩ፣ ታንክና መድፍ አስረክቡ፣ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ተባበሩ ያሉት ፊልድ ማርሻሉ ከፈለጋችሁ በሕገ መንግስቱ መሰረት መሄድ ትችላላችሁ ሲሉ ተደምጧል።

ይህ ብዙዎች ያስደነገጠው የፊልድ ማርሻሉ ንግግር የትግራይን ህዝብ የመግፋት ስትራቴጂ ነው በማለት ትችት እየቀረበባቸው ነው።

በ2014 ዓ/ም የትግራይ ሰራዊት ሰሜን ሸዋ በደረሰበት ወቅትም የአዲስ አበባ ከንቲቧ አዳነች አበቤ “ራሳቸው ያሰፈሩት አንቀፅ 39 አለ፣ በዛ መሰረት መሄድ ነው” ብሎ እንደነበር የሚታወስ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates