አፍሪካ
በኤርትራ መንግስት በቀይ ባህር ዓፋር ህዝቦች እየደረሰ ያለው ሰቆቋ የዓለም ማህበረሰብ በአስቸኳይ እንዲደርስለት አርሳዶ የተሰኘ ድርጅት ጥሪ አቀረበ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 15/11/2017፡ የቀይ ባህር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/አርሳዶ ይህንን አስቸኳይ ጥሪ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የኤርትራ መንግስት በዳንካሊያ ክልል በአፋር ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን “መንግስታዊ” ያለውን የሽብር ተግባር እንዲከላከል ጥሪ አቅርቧል።
በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ፈላጭ ቆራጭ የአገዛዝ ዘመን፣ ኤርትራ ወታደራዊ የጦር ሰራዊት ሆናለች ያለው ድርጅቱ በጭቆና፣ በጎሳ ስደት እና ያለፍርድ እስራት በመፈፀም አምባገነኑ ስርዓት የአለም አቀፍ ህግ እና የሞራል ህሊና እየተላለፈ ነው ብሏል።
እ.ኤ.አ. ከ1993 ጀምሮ በኤርትራ የሚኖሩ የአፋር ህዝቦች የተናጠል ጥሰቶች ብቻ ሳይሆን ስልታዊ፣ የተቀናጀ እና የዘር ማጥፋት ፖሊሲ እየተፈፀመባቸው ነው ሲልም ድርጅቱ ይከሳል።
የኤርትራ መንግስት በቀይ ባህር አፋሮች በስልታዊ የማጥፋት ፕሮጀክት፣ የባህል ማጥፋት እና የግዳጅ መፈናቀል ተግባራት ክየተፈፀሙበት መሆኑም አስረድቷል።
እነዚህ አስከፊ ወንጀሎች ከባድ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ናቸው ያለው አረሳዶ ከእነዚህም መካከል በአፋር ንፁሀን ዜጎች ላይ የግፍ ግድያ፣ በግዳጅ መሰወር፣ የጅምላ እስራት እና ለረጅም ጊዜ የማይታወቅ እስራት፣ ግዳጅ ብሔራዊ አገልግሎት እየደረሰባቸው ነው ብሏል። ይህም ዘመናዊ ባርነት ነው ሲል ገልፆታል።