በትግራይ ደቡባዊ ዞን እየተደረገ ያለው የአመራር ማስተካኪያ ተቃውሞ እንደገጠመው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 15/11/2017፡ በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ትእዛዝ በሰጠው አድማ በታኝ ፓሊስ የተደገፈ የስልጣን ሹምሽር እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል።
ከትናንት ሀምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው ከመቐለ ወደ ማይጨው ከተማ በተላከ የአድማ ብተና ፓሊስ ጥብቅ ቁጥጥር ስር የስልጣን ሹምሽር እየተካሄደ ያለው።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የስልጠን ሹም ሽሩ ” ሰላማዊ ነው ” ቢሉም የቀድሞ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ጨምሮ በርካቶች ድርጊቱ ” በሀይል የሚደረግ ግጭት ቀሰቃሽ የስልጣን ንጥቂያ ” ብለውታል።
በመግባባት ስልጣን ተሰጣቸው የተባሉት አመራሮችም ሹመቱ እንደማይቀበሉት በማሕበራዊ ሚድያ አስታውቋል።
የዞኑ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ በወርሃ መጋቢት 2017 ዓ.ም ከትግራይ ከወጡበት ጀምሮ የአመራር ለውጥ ያልተደረገበት አከባቢ ሆኖ ቆይቷል።
ፕሬዝዳንት ታደሰ በመግለጫቸው ከዞኑ የአመራር ቦታ የሚነሱ ሀላፊዎች በክልል የሃላፊነት ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል ብሏል።
የስልጣን ሽምሹሩ እንዲተገበር የሚያሳልጥ ፓሊስ ወደ አከባቢው ተልኳል ያሉት ፕሬዝዳንቱ
በዞኑ የለውጥ አመራር ለማድረግ ያስፈለገበት ምክንያት ቀጣይ አደጋዎች ለማስቀረትና የክልሉ የፀጥታ ችግር ለመፍታት ነው ብሏል።
መንግስት በዞኑ በግድ ማድረግ ያለበት ነው እያደረገ ያለው ስለሆነም ሂደቱ ማደናቀፍ አይቻልም ሲሉ አስጠንቅቋል።
በትግራይ ደብባዊ ዞን እየተከናወነ ያለውን ጉዳይ” በዞኑ ህዝብ ላይ የተጫነ አስገዳጅ የስልጣን ንጥቂያ ነው ” በማለት ብርቱ ትችት አዘል ፅሁፎች እየተሰራጩ ይገኛሉ።