ኢትዮጵያኢኮኖሚ

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የተካሄደው መቶ በመቶ በኢትዮጵያውያን ገንዘብ ነው ሲል የግድቡ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 15/11/2017፡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ መቶ በመቶ የተገነባው “ያለምንም የውጭ እርዳታም ሆነ ብድር በራስ አቅም”፣መሆኑን አስታወቀ።

ጽህፈት ቤቱ ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 15ቀን 2017 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ መላው ኢትዮጵያውያን ንግድቡ ግንባታ ሂደት ውስጥ “በሞራል፣ በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በዕውቀት” መሳተፈቸውን ጠቅሷል።

ከዚህ ቀደም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ባለፈው ቅዳሜ ሐሶስተኛ ጊዜ ግድቡ “በአብዛኛው በአሜሪካ ገንዘብ” የተገነባ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል።

ይህንን የፕዝዳንቱን ተደጋጋሚ አስተያየት በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት አስካሁን ይፋዊ አስተያየት ለመስጠት ተቆጥቦ ቆይቷል።

አሁን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ ግን ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ግንባታው ከተጀመረ አስራ አራት ዓመት የሆነው የግድቡ ግንባታ ወጪ ሙሉ ለሙሉ በአገሪቱ መሸፈኑን አመልክቷል።


ለግድቡ በ2017 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 30 ድረስ ብቻ “በቦንድ ግዢ እና በስጦታ” ከአገር ውስጥ 1.2 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን፣ ከአገር ውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ 95 ሚሊዮን ብር መገኘቱን ጠቅሷል።

በአጠቃላይ በተለያየ መንገድ ከአገር ውስጥ እና ውጪ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰበሰበው ገንዘብ 1.7 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ይህም ከዕቅዱ የ7 በመቶ ብልጫ እንዳለው አመልክቷል።

ኢትዯጵያ ግድቡን መገንባት ከጀመረችበት ገዜ ጀምሮ ከአገር ውስጥ በቦንድ ግዢ እና በስጦታ 20̏ ቢሊዮን ብር በላይ፣ ከዳያስፖራው ማኅበረሰብ ደግሞ 1.6 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቧን አስታውቋል።

ይህም በአጠቃላይ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም. ድረስ 23.6 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ ለግድቡ ግንባታ መዋሉን ገልጿል።

ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ የግድቡ ግንባታ መጠናቀቁን ገልጾ፣ የቀረው “ሪቫን መቁረጥ” መሆኑን በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰኔ ወር መጨረሻ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት የሕዳሴ ግድብ በመጪው አዲስ ዓመት መጀመርያ ላይ በይፋ እንደሚመረቅ መናገራቸው ይታወሳል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates