ኢትዮጵያፖለቲካ

ኦፌኮ በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ 3 ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 14/11/2017፡  በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የሚመራው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ)  የጀመረውን የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ያጠናቀቀ ሲሆን በመጪው ምርጫ ላይ ፓርቲው ያለውን አቋምም ይፋ አድርጓል፡፡

“የ2018 አገራዊ ምርጫ ላይ ያለን አቋም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነው” ያለው ፓርቲው ጨምሮም “ለተሰባበረ የፖለቲካ ሂደት እውቅና አንሰጥም” ብሏል፡፡ ኦፌኮ ያቀረባቸው ቅድመ ሁኔታዎችም

በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያለው ጦርነት በአፋጣኝና በአለም አቀፍ ታዛቢዎች በተረጋገጠ መልኩ እንዲቆምና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲጀመር፣

ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ የፖለቲካ ነፃነቶች በሙሉ እንዲከበሩና የታሸጉ የኦፌኮ ቢሮዎች እንዲከፈቱ እንዲሁም አፋኝ የሆኑ የሚዲያና የሲቪል ማህበረሰብ ህጎች እንዲሻሩና

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የህዝብን አመኔታ እንዲያገኝ ሁሉም ፓርቲዎች ሙሉ ስምምነት ላይ ተመስርቶ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር የሚሉ ናቸው፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates