አፍሪካ
የሱዳኑ የሉአላዊ ምክርቤት ፕሬዝዳንት ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሀን የሱዳን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ ማረፋቸው ተገልጿል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 14/11/2017፡ የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ጦርነቱ ከተጀመረበት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2023 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሬዚዳንቱን አይሮፕላን በካርቱም ዋና አውሮፕላን ማረፊያ ቅዳሜ ዕለት እንዳረፈ የመንግስት ሚዲያዎች ዘግቧል።
ይህ እርምጃ መንግስት ወደ ዋና ከተማዋ ለመመለስ የሚያደርገውን ጥረት ያሳያል ተብሏል።
እንዲሁም የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር በካርቱም የደረሱትን ጉዳቶች ለመገምገም የመጀመሪያ ጉብኝት አደርጓል።
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ በግንቦት ወር ከተሾሙ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋና ከተማው ጉብኝት ለማድረግ አርብ ዕለት ካርቱም ገብተዋል።
ታሪካዊ ጉዞው ያደረሰውን ሰፊ ጦርነት ለመገምገም እና የመልሶ ግንባታ ጥረቶችን ለመጀመር ያለመ ነው ሲል የመንግስት መግለጫ ገልጿል።