አፍሪካ

የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት በሱዳኑ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይል ማዕቀብ ጣለ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 14/11/2017፡ ምክር ቤቱ በግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና የሀገሪቱን ሰላም፣ መረጋጋት እና ደህንነት አደጋ ላይ በማዋል ማዕቀብ ጣለ።

ምክር ቤቱ በሱዳን ያለው አስከፊ ሁኔታ በሱዳን ጦር ሃይሎች እና ፈጣን የድጋፍ ሃይሎች መካከል ከሁለት አመታት በላይ ሲካሄድ የቆየው ጦርነት በሁለት ግለሰቦች እና ሁለት አካላት ላይ ትላንት የእገዳ እርምጃ አጽድቋል።

በአውሮፓ ህብረት የተዘረዘሩት አካላት አልካሌጅ ባንክ እና ሬድ ሮክ ማዕድን ኩባንያ ናቸው። ሬድ ሮክ የማዕድን እና ፍለጋ ኩባንያ ሲሆን፣ የዚህ እህት ኩባንያ ቀድሞውኑ በአውሮፓ ህብረት ፣ በዩናይትድ ስቴትስ እና በዩናይትድ ኪንግደም ገዳቢ እርምጃዎች ተወስኖበት የነበረ ኘው።

ኩባኒያው ለፈጣን ድጋፍ ሐይሉ የጦር መሳሪያዎችን እና ተሽከርካሪዎችን በማመቻቸት ላይ ተሳትፏል በማለት የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ማዕቀብ ጥሎበቴል።

ሁለተኛ አልካሌጅ ባንክ በአብዛኛው ከ RSF አዛዥ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ እና የቤተሰብ አባላት ጋር በተገናኙ እንደሆነ እና የ RSF ስራዎችን በገንዘብ በመደገፍ ወሳኝ ሚና ይጫወታል በማለት ምክር ቤቱ ማዕቀብ ጥሎበታል።

የአውሮፓ ህብረት ገዳቢ እርምጃዎች በ ሱዳን ሰራዊት ወታደራዊ አዛዥ አቡ አቅላ መሀመድ ካይካል ላይ እገዳ የጣለ ሲሆን፣ እሱም ቀደም ሲል ወደ RSF የከዱ እና  የጃዚራ ግዛት ገዥ የነበሩ ናቸው።

የሱዳን ጋሻ ጦር ሃይል መሪ ሆኖ በነበረበት ወቅት በዋናነት ኑባ እና ሌሎች የአፍሪካ ጎሳዎችን ያቀፈውን የካናቢን በታሪክ የተገለሉ ቡድኖችን ኢላማ በማድረግ ወንጀል ፈፅሟል ተብሏል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የ RSF ወታደራዊ መስክ አዛዥ ሁሴን ባርሻምን ላይ ማዕቀብ እንደጣለ አሳውቋል። የእነዚህ ገዳቢ እርምጃዎች የአውሮፓ ህብረት ለሱዳን ሰላም እና ተጠያቂነት ያለውን የማያወላውል ድጋፍ ያጎላል ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates