ኢትዮጵያ

የትግራይ ሲኖደስ በድጋሚ የሰላም ልኡክ ወደ አዲስ አበባ ላከ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 14/11/2017፡ “የሰላም” ልኡካን ወደ አዲስ አበባ የተላከው ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ/ም ነው።

የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ልኡኳን ቡድን ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ወደ አዲስ አበባ አምርቷል።

ልኡኩ “ሰላማዊያን ብፁዓን ናቸው” የሚል የሰላም ምልክት የያዘ ሲሆን የጉዘው ዋና ዓላማም ስለ ሰላም ለመወያየትና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ መሆኑን የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለድምፅ ወያነ ቴሌቪዥን ተናግሯል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ የሰላም ልኡካን ልኮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር መወያየቱ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ የሰላም መልዕክተኞችን እንደላከ ታውቋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates