
ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/11/2017፡ አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዛሬ እንደዘገበው የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የፕሪቶሪያ ስምምነት ተደራዳሪዎች በድጋሚ እንዲገናኙ ቢፈልጉም በአቢይ አህመድ መሰናክል ምክንያት ሊሳካ አልቻለም ብሏል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ውጥረት ባለበት ሁኔታ ተደራዳሪዎች ኡሁሩ ኬንያታ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ዘገባው አመልክቷል።
የፕሪቶሪያ ስምምነት ተደራዳሪ የሆነው ህወሓት የአፍሪካ ህብረት ስምምነቱን እንዲጠራው አፈፃፀሙን እንዲገመግምና የፖለቲካ ድርድር እንዲጀምር ደጋግሞ መጠየቁን ባለፈው ሳምንት ለተመድ በፃፈው ደብዳቤ አስትውቋል።
እንደ አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘገባ የአፍሪካ ህብረት ፎረም ለማካሄድ ያልፈለገበት ምክንያት ከአብይ አህመድ አወንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ ሊሆን ይችላል። በዘገባው ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ምላሽ አልሰጡም።