
ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/11/2017፡ ስደተኞች ትናንት ሀምሌ 10 ቀን 2017 ባደረጉት ሰልፍ አለም አቀፉ ማህበረሰብ በአስቸኳይ ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
“በምግብና መድሀኒት እጥረት እየሞትን ነው” ያሉት ሰልፈኞቹ ጨምረውም “የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባለመሆኑ ስቃያችን እየከፋ ይገኛል” በማለት አሳስበዋል፡፡ ዘላቂው መፍትሄም በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ወደቤታቸው መመለስ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ በተንድባ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ብቻ ከ400 በላይ ሰዎች በረሃብ እና በበሽታ መሞታቸው ተገልጿል።
ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ በተንድባ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ብቻ ከ400 በላይ ሰዎች በረሃብ እና በበሽታ ሞተዋል።