ፖለቲካ

የትግራይ ሽማግሌዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኣሕመድ መወያየታቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/11/2017፡ ይህ 20 አባላት የያዘ ልኡኩ የሃይማኖተ መሪዎች፣ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ፅላል ማህበረሰብ የተወከሉ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ከውይይቱ በኃላ በማህበራዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባጋሩት መልእክት ” በአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የሚደረግ ምክክርና እርቀ ሰላም ፍሬው ጣፋጭ ነው ” ብሏል።

ትናንት ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ዛሬ ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ መክረዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ  ” የኢፌዲሪ መንግስት በሽምግልና እና ምክክር ችግሮች እንዲፈቱ ቅድምያ ሰጥቶ እንደሚሰራ በተለያዩ ጊዚያት በተግባር አሳይቷል ” ብለዋል።

” ከተለያዩ የትግራይ የማህበረሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አካላት ለቀጣይ መደረክ ምቹ መደላድል የሚፈጥር ውይይት አካሂደናል ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥያቄና መልስ የታጀቡ በርካታ ጉዳዮች እንደተነሱ ገልጸዋል።

በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አተገባበር ያሉት ተግዳሮቶች እንዴት መታረም አለባቸው ፣ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ንግግሮች መቆምና መታረም እንዳለባቸው በተለይ የተፈናቃዮችና ትግራይን መልሶ መገንባት ጉዳይ የምክክሩ ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ ብለዋል።

የትግራይ ህዝብና ልሂቃን በአገሪቱ ፓለቲካና ኢኮኖሚ በብርቱ ተዋናይ የሚሆኑበት ሁኔታ መፍጠር እጅግ አስፈላጊ እንደሆነና ሌሎች ጉዳዮች ተነስው መግባባት ተደርሶባቸዋል ብለዋል።

” የፌደራል መንግስት ከህዝብ ፣ ከጊዚያዊ አስተዳደሩና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በፓለቲካ በፀጥታና ኢኮኖሚ እንዲሁም በትግራይ መልሶ ግንባታ ዙሪያ ተቀራርበን እንደምንሰራ ደገመን እረጋግጠንላችኋለን ” ሲሉ ገልጿል ጠቅላዩ።

የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ትናንት ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም በመቐለ ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ከተወያዩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ነው ዛሬ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ጋር ውይይት ያደረጉት።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates