አፍሪካ
ብርጌድ ንሀመዱ ዋና ፅህፈት ቤቱን በአሜሪካ አደረገ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/11/2017፡ በውጭ አገር የሚገኙ ኤርትራዊያንን ያቀፈውና ራሱን ብርጌድ ንሀመዱ ብሎ የሚጠራው ቡድን ዋና ፅህፈት ቤቱን በአሜሪካ ማድረጉን አፍሪካን ኢንተለጀንስ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ይህ ቡድን መጠሪያውን ‹‹ኤርትሪያን ብሉ ሪቮሉሽን ፍሮንት›› በሚል በአሜሪካ ውስጥ አስመዝግቧል፡፡ እንዲሁም ለእንቅስቃሴው እንዲረዳው ሎቢ መቅጠሩን ዘገባው ገልጿል፡፡
ብርጌድ ንሀመዱ የኤርትራን መንግስት የሚቃወም ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡