ኢትዮጵያፖለቲካ

‘’የተፈናቃየች መመለስ ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም’’ ጄነራል ታደሰ ወረደ

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/11/2017፡ “የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው” ሲሉ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ ገለፁ።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ “የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው” ሲሉ ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንንያሉት በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዳይሬክተር አንድሪው ምቦጊሪን ትላንት ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረዳ አንድሪው ምቦጊሪን ጋር በነበራቸው ቆይታ  “ያለ ደህና መጠለያ እና ምግብ ተጥለው በከፍተኛ ችግር ላይ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለአምስተኛ የክረምት ወራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ህይወታቸውነ እያሳለፉ ማየት በጣም ከባድ ነው” ሲሉ መናገራቸውን ከጽ/ቤታቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዳይሬክተር አንድሪው ምቦጊሪን በበኩላቸው በክልሉ በተካሄደው አስከፊ ጦርነት ሳቢያ ቤታቸውን ጥለው የተሰደዱ የክልሉ ነዋሪዎችን ተቋማቸው ተቀብሎ መጠለያ እና ምግበ እንዲያገኙ ማድረጉን አስታውሰው በቀጣይ በሚደረገው የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ይሁን በቀያቸው እስኪቋቋሙ ድረስ ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል መግባታቸውን መረጃው አካቷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates