ማህበራዊኢትዮጵያ

በአውሮፕላኑ አደጋ እነማን ተጎዱ?

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/11/2017፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ባጋጠመው የመንሸራተት አደጋ በሁለት ሰዎች ጉዳት መድረሱ ታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የበረራ ቁጥር ET-298  በትላንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ ተነስቶ መቐለ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ካረፈ በኋላ ከአውሮፕላን መንደርደሪያው መጠነኛ የመንሸራተት እክል አጋጥሞታል ብሏል።

አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ጊዜ ዝናብ እየዘነበ እንደነበር ያስታወሰው መግለጫው “እስካሁን ባለን መረጃ በክቡራን መንገደኞቻችን ላይ ምንም አይነት ጉዳት ያልደረሰና በሰላም ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ የተደረገ ሲሆን በሁለት የበረራ ሰራተኞቻችን ላይ መጠነኛ ጉዳት በማጋጠሙ ለተጨማሪ የህክምና ዕርዳታ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የህክምና መስጫ ተቋም  ተወስደው ከታከሙ በኋላ ወደ ሆቴል እንዲሄዱ ተደርገዋል” ሲል ገልጿል።
አየር መንገዱ ያጋጠመው ጉዳት በሁለት የድርጅቱ ሰራተኞች ነው ቢልም የመቐለ ከተማ አስተዳደር ያወጣው መረጃ ግን በአብራሪዋ እና በአንድ መንገደኛ ጉዳት እንደደረሰ የሚያመለክት ነው።

የመቐለ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ለመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ በሰጡት መረጃ መሰረት ጉዳቱ በሴት አብራሪ እና በአንዲት መንገደኛ ላይ ነው።
በአውሮፕላኑ ውስጥ ህፃናትን ጨምሮ 49 መንገደኞች፤ ሁለት አብራሪ እና ሁለት አስተናጋጅ ሰራተኞች እንደነበሩ የጠቆመው መረጃው ሆኖም በሁለቱ ሰዎች ከደረሰ አደጋ ውጪ በሰላም ወደየቤታቸው ለመሄድ ችለዋል።
አብራሪዋ ሁለት ጊዜ ለማረፍ ሙኮራ አድርጋ ወደ አየር እንደተመለሰች የሚያስረዱት ተሳፋሪዎቹ በሶስተኛ ሙኮራ ግን ከመስመር በመውጣት መሸራተቷ እና በግራ ክንፏ እንደተደገፈች አስረድቷል።
በመቐለ አየር ማረፍያ እንደዚህ ዓይነት አደጋ ሲያጋጥም የትላንቱ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates