ኢትዮጵያኢኮኖሚ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅን አፀደቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 10/11/2017፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ ያፀደቀው የተሻሻው አዋጅ በቀጣይ ዓመት ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ 26 አንቀፆች ላይ ማሻሻያ የተደረገበት ነው ተብሏል።

የተሻሻለው አዋጅ ሴቶች፣ ወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች በፖለቲካ የሚኖራቸውን ተሳትፎ የሚያጠናክር እንደሆነና ከዚህ ቀደም በነበረው አዋጅ በምርጫ ጣቢያ የነበረውን የምርጫ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴን ወደ ምርጫ ክልል እንዲሆን ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

የመራጮችን ምዝገባ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ እንዲሆን የሚያደርግ፣ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችን ያካተተና በምርጫና በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ሂደት የሚታዩ ክፍቶችን ሁሉ የሚሞላ እንደሆነም ተጠቁሟል።

የተሻሻለው አዋጅ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን የ6 ክልሎችን ድጋፍ ማግኘትን የሚያስገድድም መሆኑም ተቃውሞ ብገጥመውም አዋጁ 1394/2017 ሆኖ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates