ኢትዮጵያጤና

በአፋር ክልል የኤርታሌ እሳተ ጎሞራ እየፈነዳ መሆኑን ተገልጿል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/11/2017፡ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የጂዖሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ኖራ ያኒሚኦ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡን አስተያየት፣ እሳተ ጎሞራው መፈንዳቱን ከአካባቢው ማህበረሰብ ማረጋገጣቸውን ገልጸው፣ ለነዋሪዎቹ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፈዋል።

” እሳተ ጎሞራው እንደፈነዳ መረጃው ደርሶናል፣ ከዚህ በፊት ያልነበረ በጣም ከፍተኛ አቧራ እየወጣ ነው ” ያሉት ተመራማሪው፣ ” በአካባቢው በሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ቢያንስ እዛ አካባቢ ያለውን ህዝብ ማራቅ የሚቻልበት መንገድ ቢፈጠር ጥሩ ነው ” ሲሉ አስገንዝበዋል።

” ኤርታሌ በቀን በጣም ብዙ ሰው የሚጎበኘው ቦታ ስለሆነ ወደዚያ የሚሄዱ ጎብኝዎች ጥንቃቄ ያድርጉ፣ ምክንያቱም የሚፈጠረው ነገር አይታወቅም ” ሲሉም ተናግረዋል።

” ከዚህ በፊት ኤርታሌ ላይ እንደዚህ አይነት ነገር የተለመደ አልነበረም፣ እሳት ጎሞራ ከመፍሰስ ውጭ፣ አሁን ግን ብናኞቹ ወደሰማይ እየወጡ ስለሆነ ጉዳትም ሊያስከትል ይችላል ” ያሉት አቶ ኖራ፣ ክስተቱ እስከሚረጋጋ ድረስ ጥንቃቄ እንደሚሻ አስገንዝቧል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates