ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ በአፋር ወደሚገኘው የትግራይ ታጣቂ ሓይል መቀላቀላቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/11/2017፡ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰላም አስከባሪ አባል የነበሩ የመጀመሪያዋ ሴት ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ በአፋር ወደሚገኘው የትግራይ ታጣቂ ሓይል መቀላቀላቸው ተገለፀ።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ አባል የነበሩት ጀነራል ዘውዱ ኪሮስ በዚህ ሳምንት በአፋር ክልል ወደሚገአው የትግራይ ተጣቂ ሃይል መቀላቀላቸው ተሰምቷል።
ጄኔራል ዘውዱ የሰራዊቱን አመራር ውሳኔ ከተቃወሙት ጄኔራሎች አንዱ ነበሩ። የትግራይ ሰራዊት በአስቸኳይ መፍረስ አለበት ብለው ከሚያምኑ መሪዎችም አንዷ ናቸው።
ጄኔራል ዘውዱ ኪሮስ ቀደም ሲል በተካሄደው መድረክ ላይ “ሠራዊቱ እንዲፈርስ የማይፈልጉት ከአጃቢዎቻቸው ጋር መኖር ስሚፈልጉ ነው” በማለት መተቸታቸው ይታወቃል።
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር ከተለወጠ በኋላ በጄኔራል ታደሰ ወረዳ በሚመራው ካቢኔ ውስጥ ላለፉት 3 ወራት የማህበራዊ ጉዳይና መልሶ መቋቋም ቢሮ ኃላፊ ሆና ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወሳል።
በርካታ ታጋዮች በአፋር ክልል እራሱን “የሰላም ሃይል” ብሎ ከሚጠራውን ጦር ለቀው ወደ ትግራይ እየተመለሱ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ። በአንፃሩ ጀነራል ዘውዱ ጦሩን ተቀላቅለዋል ተብሏል።
በአፋር እና በፀለምት የሚገኘው ሃይል ሙሉ በሙሉ በፌደራል መንግስት የሚደገፍ እንደሆነ እና አላማውም ሙሉ በሙሉ መጠለፉን በቅርቡ ወደ ትግራይ የተመለሱ ታጋዮች መናገራቸው ይታወሳል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጄነራል ታደሰ ወረዳ ሰሙኑን በተከበረው የትግራይ ሰማእታት የማጠቃሊያ በዓል ተገኝተው “ከአፋር የሚደርስ ማንኛውም ትንኮሳ የፌደራል መንግስት ወይም የአፋር ክልል ተደርጎ ነው የሚወሰደው፤ ተጠያቂም የፌደራል መንግስት ነው” ማለታቸው ይታወሳል።