አፍሪካፖለቲካ

82 የአይ ኤስ አይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/11/2017፡ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 82 የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።

አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ትላንት ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በፑንትላንድ የሚንቀሳቀሰው የአይ ኤስ የሶማሊያ ክንፍ በተለያዩ ሀገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ ለመስፋፋትና የሽብር ቡድኑን ሴሎች ለመመስረት የሚያደርገውን ጥረት በተመለከተ የመረጃ ስምሪትና ጥናት ሲደረግ ቆይቷል።

በዚህም የሽብር ቡድኑ በፑንትላንድ አሰልጥኖ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሰማራቸው 82 ተጠርጣሪዎች ተለይተው ከፌዴራል ፖሊስና ከክልል የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተመላክቷል።

ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ፣ አዳማ፣ ሃሮማያ፣ ሻሸመኔ፣ ባሌ፣ ጅማና ሻኪሶ ከተማ ዙሪያ፤ በአማራ ክልል ከሚሴ አካባቢ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞንና ሃላባ ቁሊቶ ከተማ፤ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማና በሐረሪ ክልል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates