ማህበራዊኢትዮጵያ

ወደ ትግራይ ያመሩት የሃይማኖት መሪዎች ውይይቱ ለሚድያዎች በዝግ እንዲደረግ መጠየቃቸው ኣነጋጋሪ ሆኗል።

የሃይማኖት መሪዎቹ ከክልሉ ግዝያዊ አስተዳደር ጄነራል ታደሰ ወረደ ተወያይቷል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/11/2017፡ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሚመራ ልዑክ ከትግራይ ክልል መሪዎች ጋር  በመቐለ ተወያየ።

የሃይማኖት ልኡኳኑ ወደ መቐለ ያመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኣህመድ “የሃይማኖት መሪዎች በትግራይ ጦርነት እንዳይጀመር አሁን ስራችሁ ጀምሩ” ማለታቸው ተከትሎ ነው።

የሃይማኖት አባቶቹ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ እና ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች ተወካዮች ጋር መክሯል።

ሆኖም የተወያዩባቸው ዝርዝር ጉዳዮች እስካሁን አልወጡም፤ ምክንያቱ ደግሞ ውይይቱ ለሚድያዎች ዝግ በመሆኑ ነው ተብሏል። ይህን ተከትሎ ስለሰላም እየተወያየህ ለምን ለሚድያ ዝግ ይሆናል የሚሉ ትችቶች እየተሰሙ ነው።

የሃይማኖት ተወካየቹ በመቀጠልም ከህወሓት እና የትግራይ ሰራዊት አመራሮች እንደሚወያዩ ይጠበቃል። ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የተላከው የሃይማኖት ተወካዮች ቡድን ከ7 የተለያዩ ተቋማት እያንዳንዳቸው 3 ተወካዮች የያዘ መሆኑን ታውቋል።

ልዑኩ ወደ ትግራይ ያመራው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ “ትግራይ ወደ ግጭት፤ ወደ ጦርነት እንዳይገባ በሀገሪቱ የሚገኙ የሐይማኖት  አባቶች በአቸኳይ ስራችሁን አሁን ጀምሩ፤ ከተጀመረ በኋላ ብትናገሩ ዋጋ የለውም” ሱሊ ካስጠነቀቁ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates