አሜሪካኢትዮጵያ

ፕሬዝደንት ትረምፕ በኢትዮጵያ እና ግብፅ መሀል ያለውን አለመግባባት ‘በፍጥነት’ እንደሚፈቱት ተናገሩ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ አሜሪካ የግድቡን ወጪ እንደቻለች በድጋሜ የጠቀሱት ፕሬዝደንቱ የናይል ወንዝ የግብፅ ‘ህይወት’ መሆኑን ሲናገሩ ተደምጠዋል።

“ይህንን ደግሞ መውሰድ እጅግ አስገራሚ ነው፣ ይህንን በፍጥነት እንፈታዋለን” በማለት ተናግረዋል። ይሁንና ግድቡ ለኢትዮጵያ ያለውን ጥቅም በጥቂቱም እንኳን ሲጠቅሱ አልተሰሙም።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትናንት ሐምሌ 7፣ 2017 ዓ/ም በዋይት ሀውስ ከኔቶ ዋና ፀሀፊ ማርክ ሩቲ ጋር ባደረጉት ስብሰባ “አሜሪካ ለግድቡ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች” ብለው እንደሚያስቡ እና ለግብፅ የውሃ አቅርቦት ስጋት እንደሆነ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት በሰኔ ወር የተሰጡትን ተመሳሳይ አስተያየቶችን ተከትሎ ሲሆን፣ በጊዜው  አሜሪካ ለግድቡ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች እናም ወደ ናይል የሚፈሰውን የውሃ መጠን “በከፍተኛ ሁኔታ” ይቀንሳል በማለት የተሳሳተ መረጃ ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ህዝብ በህዝባዊ መዋጮ እና በአገር ውስጥ ሀብቶች የተገነባ፤ ለግብፅ የውሃ ደህንነት ምንም አይነት ስጋትም እንደማይፈጥር የኢትዮጵያ መንግስት መግለፁ የሚታወስ ነው፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates