ማህበራዊአውሮፓ

ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ሠራተኞቹ በኢትዮጵያ መከላከያ መገደላቸውን አስታወቀ::

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ ከአራት ዓመታት በፊት በትግራይ ጦርነት ወቅት በክልሉ የሰብዓዊ ተልእኮ ላይ የነበሩ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን (MSF) ሶስት ሰራተኞች “ሆን ተብሎ እና በግልጽ ተለይተው” በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት “ያነጣጠረ ግድያ” እንደተፈጸመባቸው ድርጅቱ አስታወቀ።

ድርጅቱ ይህን ያስታወቀው ከአራት ዓመታት በፊት፣ ሰኔ 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሶስት ሰራተኞቹ ላይ “ሆን ተብሎ ያነጣጠረ” ግድያ መፈጸሙን አስመልክቶ በውስጣዊ ምርመራ የደረሰባቸውን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።

ሶስቱ ሰራተኞች የ35 ዓመቷ ስፔናዊቷ ማሪያ ሄርናንዴዝ ማታስ እንዲሁም ሁለቱ ኢትዮጵያውያን የ31 ዓመቱ ቴዎድሮስ ገብረማርያም እና የ32 ዓመቱ ዮሐንስ ሃለፎም ረዳ ናቸው።

የሶስቱ ሰራተኞች አስክሬን ከግድያው ማግስት ይጓዙበት ከነበረበው ተሽከርካሪ በ400 ሜትሮች ርቀት የተገኘ ሲሆን፤ ተሽከርካሪያቸው ደግሞ በተደጋጋሚ በጥይት ተመትቶ እንዲሁም ተቃጥሎ ነበር።

ኤም.ኤስ.ኤፍ ባካሄደው ምርመራ “ጥቃቱ ሆን ተብሎ እና በግልጽ በሚታወቁ ሶስት የረድኤት ሰራተኞች ላይ ያነጣጠረ ግድያ መሆኑን” እንዲሁም “የኤም.ኤስ.ኤፍ ሰራተኞች በተገደሉበት በዚሁ መንገድ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት ኮንቮይ እንደነበረም” ማረጋገጡን ገልጿል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates