
ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት በሕገ-ወጥ መንገድ ሀገር ውስጥ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ12 ሺሕ 127 በላይ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል::
ከውጭ ሀገር ዜጎቹ በተጨማሪ፤ ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተገናኘ ዜጎችን ለእንግልት የዳረጉና ብልሹ አሰራር ውስጥ የተገኙ 26 የተቋሙ ሠራተኞች በሕግ ተጠያቂ መደረጋቸው ተነግሯል፡፡
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት 3 ሺሕ 868 ሰዎች የተጭበረበረ ሰነድ በመጠቀም ፓስፖርት ለማውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር በማዋል በሕግ ተጠያቂ መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለፉው አንድ ዓመት በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ሰዎች መካከል 2 ሺሕ 77 ሃሰተኛ ሰነድ በማቅረብ፣ 275 ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ ፓስፖርት ለማውጣት በመሞከር እንዲሁም የተቀሩት በተለያየ መንገድ ለማጭበርበር ሲሞክሩ የተያዙ መሆናቸውን ገልጸዋል።