
ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ በተገባደደው ዓመት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሁኔታ በሚመለከት ይፋ ባደረገው ሪፖርት፣ ከ55 እስከ 80 በመቶ የሚሆነው ከኢትዮጵያ የሚወጣው ገንዘብ፣ ሕጋዊ ባልሆነ የገቢና የወጪ ንግድ ልውውጥ በኩል ነው።
ይህም ከጠቅላላ የአገሪቱ ምርት (GDP) 2.2 በመቶ ያሳጣታል ብሏል፡፡ እንዲሁም ከስድስት እስከ 23 በመቶ የሚሆነውን አጠቃላይ የኢትዮጵያ ንግድ የሚሸፍን መሆኑን አስታወቀ፡፡
በሕገወጥ መንገድ የሚደረገው የገንዘብ ፍልሰት ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት 2.2 በመቶውን እንደሚያሳጣ የሚገልጸው ሪፖርቱ፣ ይህም ከአሥር እስከ 30 በመቶ የመንግሥት ገቢ እንደሆነ ያሳያል፡፡
ለሕገወጥ የገንዘብ ፍልሰቱ ሦስት ምክንያቶች መኖራቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ የመጀመሪያው ወደ ውጪ የሚላኩ ዕቃዎች ከሚያወጡት ገንዘብ በታች እንደሆነ የሚያስመስል ደረሰኝ ማቅረብ ዋነኛው ነው።