አፍሪካኢትዮጵያዲፕሎማሲ

“ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ገፅቷ እያበላሸች ነው” ስትል ግብፅ ዛተች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ የግብፅ የውሃና መስኖ ሚኒስትር ዶ/ር ሃኒ ሰዊላም ከኤምቢሲ አረቢያ ቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ አዲስ አይደለም፤ እነዚህን የእናስመርቃለን ወሬ ከዚህ በፊትም ሰምተናል፣ እና ኢትዮጵያም ገፅታዋን በአለምአቀፍ ደረጃ ለማጥፋት እየሞከረች እንደሆነ ግልፅ ነው” ብለዋል።

በመቀጠልም የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚንስትር “በግብፅም ሆነ በሱዳን ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳይደርስ ኢትዮጵያ አስገዳጅ ስምምነት እንድትፈርም እጠይቃለሁ” በማለት ታላቁን ህዳሴ ግድብ “አለም አቀፍ ህግን የጣሰ ህገ-ወጥ ግድብ” በማለት ከሷል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማጠናቀቂያ ዜና በካይሮ ውስጥ ጠንካራ ስሜቶችን እንደቀሰቀሰ ይገባኛል ያሉት ሚኒስትሩ ነገር ግን የግብፅ ትችቶች እራሱን እንከን የለሽ አድርጎ በመሳል ኢትዮጵያን እና ግድቧን ለመናድ የሚደረግ ሙከራ ስህተት ነው ብሏል።

ግብፅ የሶስትዮሹ ድርድር ወደጎን በመተው ኢትዮጵያን ለማወክ የተለያዩ ጥረቶች እያደረገች እንደምቴገኝ ይገለፃል። ክእነዚህ ጥረቶች ሶማሊያንና ኤርትራን ከጎኗ በማሰለፍ ኢትዮጵያ የበር ባህር እንዳታገኝ ማድረግ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates