
ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚድያ ዳሰሳ በማቅረብ ያታወቅ የነበረው ታደሰ ሚዛን ባደረበት ህመም ከዚህ ዓለም መለየቱ ተሰምተዋል፡፡
በ1963 በትግራይ ውቅሮ የተወለደው ታደሰ ሚዛን ሐምሌ 2 ቀን 2017 በሲያትል አሜሪካ ማረፉ ተገልፀዋል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን የማስተርስ ድግሪ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪውን በአሜሪካ ያገኘው ታደሰ ሚዛን፣ በአገራችን ግንባር ቀደም ከሚባሉ ጋዜጠኞች አንዱ ነበር።
በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከጋዜጠኝነት እስከ የዜናና ወቅታዊ ጉዳዮች ዳይሬክተርነት ያገለገለው ታደሰ ሚዛን “የሚዲያ ዳሰሳ” በሚለው ጥልቅ ትንታኔ ይበልጥ ይታወቅ ነበር።
ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን በግል ህይወቱ ከብዙ ሰዎች ጋር ትርጉም ያለው ነገር በመለዋወጥ የንባብ ባህሉን ከፍተኛ እንደነበር ይገለፃል፡፡
ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን ባደረበት ህመም ከዚህ አለም በሞት መለየቱን ተገልፀዋል።
ኢትዮ ሞኒተር ለመላው ቤተሰቦቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡