ኢትዮጵያ

ከትግራይ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽማግሌ ሊላክ ነው፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የትግራይን የሰላም ፍላጎት ለማስረዳት ወደ  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሽማግሌዎችን እንልካለሁ አለ።

የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ትግራይን አስመልክቶ የሰጡት መግለጫ እጅግ አሳሳቢና የትግራይን ወቅታዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው ብሏል።

የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የአገር ሽማግሌዎችን ልኮ የትግራይን ሕዝብ ወቅታዊ ሁኔታና ሰላማዊ ፍላጎት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚያስረዳ አስታውቀዋል። የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ እንዳስታወቀው የትግራይ ህዝብ ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ መንግስት እና አጋሮቹ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ግፍና በደል ሲደርስበት እንደቆየ አስታውሰዋል። በአለም አቀፍ አስታራቂዎች የተፈረመውን የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባለማድረጉ የትግራይ ህዝብ በተለይም ተፈናቃዮቹ ለሞትና ለከፋ ስቃይ መዳረጋቸው ገልፀዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ስለ ትግራይ የህዝብ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰጡትን ማብራሪያ የትግራይ ህዝብን ለበለጠ ጥፋት እና አደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ ጠቅሰዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የትግራይን ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው ሲልም ወቅሰዋል።

ስለሆነም የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የአገር ሽማግሌዎችን በመላክ የትግራይ ሕዝብ ወቅታዊ ሁኔታና ሰላማዊ ምኞት እንደሚያስረዱ የሃይማኖት አባቶቹ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates