አፍሪካኢትዮጵያዲፕሎማሲ

ኢትዮጵያና ሶማሊያ የጀመሩት ድርድር መቋረጡ ተዘገበ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ አፍሪካን ኢንተለጀንስ ትናንት ባሰራጨው ዘገባ እንዳመለከተው በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ተከትሎ ቱርክ የሽምግልና ሚና መጫወቷን ይታወሳል፡፡

ድርድሩ በይደር የተቋጨ እንደሆነና በእንጥልጥል ላይ እንደሚገኝ የገለፀው ዘገባው ሁለቱ አገራት የቴክኒክ ስምምነት ለማድረግ በቀጠሮ ላይ እንደነበሩ ጠቅሷል፡፡ በዚህ የቴክኒክ ድርድር ላይ ባለመስማማታቸው ድርድሩ መቋረጡን ምንጮቹን ጠቅሶ አስረድቷል፡፡

የቴክኒክ ድርድሩ ኢትዮጵያ የባህር በር በምታገኝበት መንገድ ላይ ነበር፡፡ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ውዝግብ ሊፈጠር የቻለው ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችውን የወደብ ኪራይ ስምምነት ተከትሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በጉዳዩ ላይ ቱርክ ጣልቃ በመግባት ሁለቱን አገራት ለማስማማት የቻለች ሲሆን ስምምነቱም በቀጣይነት የቴክኒክ ድርድር ላይ ለመድረስ ነበር፡፡ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሓሙድ ወደ አዲስ ኣበባ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ሞቋድሾ ጉብኝ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates