ኢትዮጵያኢኮኖሚ

የአለም ባንክ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ “የማይታወቅ/unclassified” የሚል ምድብ ውስጥ ማስቀመጡን ታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ የአለም ባንክ የአለማችንን አገራት በሙሉ ያካተተ አዲስ የኢኮኖሚ ሪፖርት አውጥቷል፡፡ የሚቀጥለውን በጀት አመት ማለትም ከጁላይ 2025 እስከ ጁን 2026 ያለው ጊዜ በሚመለከተው በዚህ ሪፖርት የአለም አገራት በ4 ምድቦች ከፋፍሎ አስቀምጧቸዋል፡፡

እነዚህም ዝቅተኛ፣ መካከለኛ ዝቅተኛ፣ ከፍተኛ መካከለኛና ከፍተኛ የሚሉ ምድቦች ናቸው፡፡ የአገራትን ገቢ መሰረት ባደረገው በዚህ ዝርዝር ውስጥ የአለም ባንክ ኢትዮጵያን በ4ቱም ምድቦች ውስጥ ሳያካትታት ቀርቷል፡፡ ሪፖርቱ “የማይታወቅ/አንክላሲፋይድ” በሚል ያላካተታቸው ኢትዮጵያንና ቬኒዙዌላን ብቻ ነው፡፡

እንደአለም ባንክ ሪፖርት “አንክላሲፋይድ” በሚል የሚጠቀሱት አገራት አመታዊ ብሄራዊ ምርታቸውን የሚመለከተው መረጃ በአግባቡ ያልሰፈረ ወይንም የተሳሳተ ከሆነ ነው፡፡ የአለም ባንክ ኢትዮጵያን በዚህ ኢኮኖሚያቸው የማይታወቅ በሚል ከአለማችን 2 አገራት አንዷ አድርጎ ያስቀመጠው በባንኩና በኢትዮጵያ መካከል ጠንካራ የብድር ስምምነት እየተካሄደ ባለበት ወቅት መሆኑ በርካታ የኢኮኖሚ ታዛቢዎችን አስገርሟል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates