አፍሪካ
በኬንያ-ኡጋንዳ ድንበር 108 ኤርትራውያን መያዛቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ ቅዳሜ እለት በኬንያ-ኡጋንዳ ድንበር በሎኪቶኒያላ አካባቢ 108 የኤርትራ ዜጎች ተጥለው ከተገኙ በኋላ የዌስት ፖኮት ባለስልጣናት በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተጠርጥረው የተጠረጠሩበትን ጉዳይ በማጣራት ላይ ናቸው ይላል መረጃው።
ቡድኑ ሴቶች፣ ወንዶች እና 13 ታዳጊዎች ያሉት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአላሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኙም አስታውቋል።
በርካታ ኤርትራዊያን ወጣቶች ማቆሚያ ለሌለው የብሄራዊ ውትድርና በመሸሽ ወደ አውሮፓ አገራት ለመሄድ ኡጋንዳን አቶ ንደ መሸጋገሪያ እንደሚጠቀሙበት ይታወቃል።