
ኢትዮ ሞኒተር፡ 01/11/2017: የሱዳን ባለስልጣናት ከተማይቱን ከወታደራዊ ሃይል መልሶ ከተቆጣጠረ በኋላ በዋና ከተማይቱ ካርቱም ጎዳናዎች እና ቤቶች የተገኙ 3ሺ 800 አስከሬኖችን ቀብረናል ሲሉ የፎረንሲክ ባለስልጣን ሃላፊ አስታውቀዋል።
ለወራት በዘለቀው ከባድ የከተማ ጦርነት በርካታ ነዋሪዎች በሁከቱ ተገድለው ወደ መቃብር ቦታ መድረስ ባለመቻላቸው ሟቾችን በየቤቱና በየአደባባዩ በጊዜያዊ መቃብር እንዲቀብሩ አስገድዷቸዋል።
የፎረንሲክ ባለስልጣን ኃላፊ ሂሻም ዘይን አል-አቢዲን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንዳሉት በግንቦት ወር ካርቱምን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ካወጀ በኋላ ቡድኖች መላካቸው እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የጅምላ መቃብሮች ማግኘታቸውንም አስታውቀዋል። ከተጎጂዎቹ መካከል ብዙዎቹ ከተማዋን በሚቆጣጠሩበት ወቅት በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች እንዲሰወሩ እና እንዲገደሉ ተደርገዋል ተብሎ ይታመናል።
በኦምዱርማን ከተማ አሮጌ ሰፈሮች ውስጥ የመቃብር ቦታዎችን ለመቃኘት የፎረንሲክ፣ የጸጥታ እና የአካባቢ ባለስልጣናትን ያካተተ ኮሚቴ ተቋቁሟል ሲል ዘይን አል-አቢዲን ተናግረዋል።