መካከለኛ ምስራቅአሜሪካ

ትራምፕ ለኖቤል የሰላም ሽልማት እጩ መሆናቸው ተሰማ። 

ኢትዮ ሞኒተር፡ 01/11/2017:  የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በዋይት ሀውስ ተገናኝተዋል ተወያይቷል።

ሁለቱ መሪዎች በእስራኤልና ሀማስ መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም እና የተኩስ ስምምነት ላይ መድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸው ከዋይት ሀውስ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በዋይት ሀውስ ባደረጉት ንግግር  ዶናልድ ትራምፕ  ለኖቤል የሰላም ሽልማት እጩ አድርገው ማቅረባቸውን ገልጸዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኖቤል የሰላም ሽልማት ኮሚቴ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት እጩ በማድረግ የላኩትን ደብዳቤ ለትራምፕ አቅርበዋል።

ኔታንያሁ “በብዙ አገሮች በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን እየሰሩ ነው” በማለት ትራምፕን አሞካሽተዋል። “ሽልማቱ ይገባዎታል፣ እናም ሊያገኙት ይገባል” ሲሉም ነው ኔታንያሁ የተናገሩት ።

ትራምፕ በበኩላቸው ይህ ከኔታንያሁ መምጣቱ “ትልቅ ትርጉም አለው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል ።
ትራም በ2019 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኖቤል ሰላም ሽልማት ከወሰዱ በኃላ “እኔ ባመጣሁት ሰላም የኢትዮጵያ መሪ ተሸላሚ ሆነ” ማለታቸውን ማነጋገሪያ ሆኖው እንደነበር የሚታወስ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates