
ኢትዮ ሞኒተር፡ 01/11/2017: የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ሰጭዎች በሱዳን ያለው ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን አስጠንቅቀዋል፣ ብጥብጡ በቀጠለ ቁጥር፣ የምግብ እና ውሃ አቅርቦት በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቋል።
በተለይም በሰሜን ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ኤል ፋሸር፣ በተቀናቃኝ ጦር ሃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለውን ግጭት ሰብአዊ ቀውሱ እጅግ የከፋ እንዲሆን አድርጎታል ብሏል።
የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በኒውዮርክ በነበረው መግለጫ ላይ በኤል ፋሸር የሚገኙ ሰዎች “እጅግ ከፍተኛ የምግብ እና የንፁህ ውሃ እጥረት እያጋጠማቸው ነው፣ ገበያዎች በተደጋጋሚ ተቋርጠዋል።
በመላው ከተማ 40 በመቶ የሚጠጉ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት በከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጦት እየተሰቃዩ እንደሚገኙም ገልጿል። ፣
በሱዳን ከፍተኛ የሰብኣዊ ቀውስ ባጋጠመበት በዚህ ወቅት የሱዳኑ ሉአላዊ ምክርቤት ሊቀ መንበር ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን በመላው አገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲጀመር አዟል። ዘመቻው የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይሉን መሉ ለሙሉ ለመደምሰስ ያለመ መሆኑን ተገልጿል።