አሜሪካኢኮኖሚ

አሜሪካ ወደ ብሪክስ የሚቀላቀሉ አገሮች ላይ ዝታለች፡፡

"አሜሪካ ከብሪክስ ጋር በሚሰለፉ ሀገራት ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ትጥላለች" ብለዋል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ 17ኛው የብሪክስ ጉባዔ የሰላም፣ የጸጥታ እና ዓለም አቀፍ አመራር መድረክ በብራዚል በሪዮ ዲ ጄኒሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም የሁለት ቀናት ስብሰባ እያደረጉ ያሉት የብሪክስ መሪዎች በዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ የንግድ ግጭቶችና ጂኦፖለቲካል ውጥረቶች እየተባባሱ በመጡበት ወቅት ጥምረቱን የዲፕሎማሲ መድረክ አድርገው አስቀምጠዋል።

የብሪክስ ሀገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች ዕሁድ እለት በሰጡት መግለጫም፤ ታሪፍ ለዓለም ኢኮኖሚ ስጋት መሆኑን በመግለጽ “በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ እና የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ እርግጠኛ አለመሆንን አስከትሏል” ሲሉ ነቅፈዋል።

ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ “ከብሪክስ ፀረ-አሜሪካ ፖሊሲዎች ጋር የሚሰለፍ ማንኛውም ሀገር ተጨማሪ 10 በመቶ ቀረጥ ይከፍላል። ለዚህ ፖሊሲ ምንም ልዩ ሁኔታዎች አይኖሩም” ሲሉ አስፈራርተዋል።

ሀገራት ከአሜሪካ ጋር የታሪፍ ውል የሚስማሙበት ቀነ ገደብ ለሐምሌ 2 ቀን 2017 ተይዞ የነበረ ቢሆንም፤ የአሜሪካ ባለስልጣናት አሁን በነሀሴ ወር መጀመሪያ ላይ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates