
ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ በአገራቸው ጦር የሚደገፉ የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ለም የሱዳን የእርሻ መሬቶችን አዲስ ወረራ በማድረግ የአካባቢውን ገበሬዎች ከማሳቸው በማፈናቀል እና የሱዳን የውስጥ ጦርነትን ምክንያት በማድረግ ሉአላዊነቴን ወርዋል ስትል ሱዳን ከሳለች፡፡
የምስራቅ ሱዳን አስተባባሪ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝደንት ሙባረክ አልኑር “የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ወደ ሱዳን መሬቶች ገብቷል” ሲሉ ለሱዳን ትሪቡን የዜና አውታር ተናግረዋል። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት እና ወታደራዊ ድንበሩን ለመጠበቅ እና የመንግስት ቁጥጥርን እንደገና ለማቋቋም “አስፈላጊ እርምጃዎችን” እንዲወስዱ ጠይቋል ባለስልጣኑ፡፡
የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የሱዳን አቻዎቻቸውን ካባረሩ በኋላ በኢትዮጵያ ጦር ጥበቃ ሥር ያለውን መሬት በንቃት እያጸዱ ነው ሲሉ አል ኑር ተናግሯል።
የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ዙሪያ ያለው ነገር ባይኖርም የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግን ”ኢትዮጵያ የአልፋሺጋ መሬትዋን ኣስመለሰች” የሚል ነው፡፡ የአልፋሺጋ መሬት የኢትዮጵያ ሰራዊት በትግራይ ጦርነት ተጠምዶ እያለ በሱዳን ሃይሎች እንደተያዘ ይገለፃል፡፡ በዚያን ወቅት የተለያዩ ሚድያዎች የኢትዮጵያ መሬት በሱዳን ተወሮ ለምን መንግስት ዝም ኣለ በማለት ሲጠይቁ የነበሩ ሲሆን ”የውስጥ ጉዳያችን ከጨረስን በኃላ በድርድር እናስመልሰዋለን” በማለት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ይናገሩ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡