ዲፕሎማሲ
ቻይና ንግድን እና ኢንቨስትመንትን ከኢትዮጵያ ጋር ለማሳደግ ዝግጁ መሆኗ ገለፀች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ ከፍተኛ ጥራት ያለው የቤልት ኤንድ ሮድ ትብብር ዋና ፕሮጀክት የሆነውን የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር ዘላቂ ልማት ለማስተዋወቅ እና የሁለትዮሽ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ለማስፋት ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ትናንት ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ይህን ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በብሪክስ ስብሰባ በተነጋገሩበት ወቅት ነው፡፡
ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በመሰረተ ልማት፣ በአዳዲስ የኢነርጂ ተሽከርካሪዎች፣ በአረንጓዴ ኢንዱስትሪዎች፣ በኢ-ኮሜርስ እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትብብሯን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆንዋም አረጋግጠዋል፡፡ አንዲሁም በቱሪዝም፣ በወጣቶች ዕድል ፈጠራ፣ በትምህርት እና በሌሎችም ዘርፎች ትብብሯን ለማጠናከር ትሰራለች ሲሉ ሊ ተናግሯል።
የብሪክስ አባል አገራት ስብሰባ በብራዚል እተካሄደ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም በስብሰባው ታድመዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ብሪክስን ከተቀላቀሉት 6 አገሮች ኢትዮጵያ አንደዋ ነች፡፡