
ኢትዮሞኒተር፡ 27/10/2017፡ ግብፅ ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ ላይ የወሰደችውን ‘የአንድ ወገን’ እርምጃ እንደማትቀበል አስታወቀች።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቢሊዮን ዶላሮች የፈጀውን ፕሮጀክት አሁን መጠናቀቁን እና በመስከረም ወር በይፋ እንደሚመረቅ ትላንት ለፓርላማ ካስታወቁ በኋላ ግብፅ የተቃውሞ ድምፅ አሰምታለች። ግብፅ ኢትዮጵያ የምትወስደውን “አንድ-ጎን” ብላ የጠራችውን ተግባር እንደማትቀበል ትላንትና አስታውቃለች።
በ4 ቢሊዮን ዶላር በጀት እ.አ.አ በ2011 የተጀመረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ሲሆን 1.8 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው እና 145 ሜትር ከፍታ ያለው ነው።
ኢትዮጵያ ግድቡ የልማትና የኤሌክትሪፊኬሽን ግቦቿ ዋና ማዕከል አድርጋ ትመለከታለች። ነገር ግን ግብፅ እና ሱዳን በውሃ አቅርቦታቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ስጋት ሲያነሱ ቆይተዋል።
የግብፅ የውሃ ሀብት ሚኒስትር ሃኒ ሰዊላም ከዲፕሎማቶች ጋር ባደረጉት ቆይታ “ግብፅ በኢትዮጵያ ልማትን ለማስፈን የሚደረገውን ማንኛውንም አይነት ጥረት ውድቅ ታደርጋለች” ብለዋል። ግብፅ አሁን “የአንድ ወገን” ውሳኔ ብትልም ይካሄድ ከነበረው የሶስትዮሽ ወይይት ራሷ መውጣትዋ ይታወሳል።